በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ቅንጅታዊ አሰራር አገልግሎትን ለማሻሻል ያለመ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

ሚያዚያ 28/2017ዓ.ም(ኢሚ) የውይይቱን መነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ታምርት ፕሮጀክት ፅ/ቤት አስተባባሪ አያና ዘወዴ(ዶ/ር) እንደገለፁት በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ቅንጅታዊ አሰራር የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የአምራች ኢንዱስትሪውን ምርታማነት የማምረት አቅም አጠቃቀሙን ማሻሻል ላይ ያለመ ውይይት ተካሄዷል።

በውይይቱ ላይ በጋራ መምከር፣ ተግዳሮቶች የሚፈቱበት አቅጣጫ ማሰቀመጥ እና ወደፊት በሚሰሯቸው ስራዎች ላይ የጋራ መግባባት መድረስና የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት አለብን ብለዋል።

እንደ ተቋም አሰራራችንን ግልፅና ቀልጣፋ በማድረግ እንደ ፋይናስ ጉሙሩክ ቴክኖሎጂ እና ቢዝነስ ድጋፍ አገልግሎታችንን በመስጠት የአምራች ዘርፉን መደገፍ ፣ አሰተማማኝ የሎጀስቲክ አገልግሎት በመሰጠት የግበሃት እና ሸቀጦች ፍሰት ማሳለጥ ፣ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመጠቀም የአምራች ዘረፉ የሚያገጥመውን ችግር መፍታት ላይ ትኩረት አድረገን እየሰራ ነው ብለዋል ።

በተጨማሪም አምራች ኢንዱስትሪውን የአንድ መስኮት አገልግሎት ተጠቃሚ የሚሆንበት የአሰራር ስረዓት ተመቻችቷል።

በፓናል ውይይቱ ላይ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች ፣ታዋቂ ሙሁራንና ሊቃውት ፣የግሉ ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post