አንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለአምራች ኢንዱስሪዎች ማቅረብ ተችሏል (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ)

ሚያዚያ 28/2017 (ኢሚ) ይህ የተገለጸው በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊና ቅንጅታዊ አሰራር የአምራች ኢንዱስሪውን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ማሻሻል በሚል ሀሳብ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ ሲሆን የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ ላለፉት ሶስት አመታት ከዘጠኝ ወር ጊዜ ውስጥ አንድ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ለአምራች ኢንዱስሪዎች ማቅረብ መቻሉን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ገልፀዋል።

ይህ የ12 በመቶ ዕድገት እንዳለው ፕሬዘደንቱ ገልፀዋል።

በባንኮች ከቀረበው ብድር 21 በመቶ የሚሆነው ለአምራች ኢንዱስትሪዎች መቅረቡን የጠቆሙት ፕሬዘዳንቱ ለዘርፉ ከሚያስፈልገው መጠን አንፃር በቂ ባይሆንም ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ለአምራች ኢንዱስሪው እየቀረበ ያለው ብድር በአነስተኛ ወለድ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዘዳንቱ ባንኩ በተያዘው በጀት አመት የዘጠኝ ወራት ውስጥ 43 ቢሊዮን ብር ብድር ማቅረብ መቻሉንና አፈፃጸሙም ከአምናው በጀት አመት አንፃር ከ95 በመቶ በላይ ዕድገት ማሳየቱን አክለዋል።

ባንኩ ጀማሪ ቢዝነስ አንቀሳቃሾችንና ሥራ ፈጠሪዎችን ለማበረታታት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ፕሬዘደንቱ ጠቁመዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post