የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት በማምረት ውጤታማ እንድንሆን አስችሎናል (አምራቾች)

ሚያዚያ 28/2017 (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተኪ ምርት በማምረት ውጤታማ አንድንሆን አስችሎናል ሲሉ በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከሚያዚያ 25 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም የሚቆየውን የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል።

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ከ288 በላይ አምራቾች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በኤክስፖ ምርቶቻቸውን ያቀረቡ በጨርቃጨርቅ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አምራቾች እንዳሉት ኤክስፖው ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post