የአምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ በርካታ የህግ ማእቀፎች እና የአሰራር ማሻሻያዎች እንዲሁም የዲጂታይዜሽን ስራዎች ተሰርተዋል።
ሚያዝያ 28/2017(ኢሚ) በሶስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አራተኛ ቀን ውሎ "በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊና ቅንጅታዊ አሰራር የአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ አምራች ኢንዱስትሪና አስመጪዎች በልዩነት የሚስተናገዱበት የቀረጥና ታክስ ክፍያ የሕግና የአሰራር ማሻሻያ መደረጉን አስታውቀዋል።
በማሻሻያው አምራቾች የገንዘብ እጥረት ቢያጋጥማቸው ዋስትና በማስያዝ የማምረትና ዕቃ የማጓጓዝ ስራቸው ሳይደናቀፍ እስከ ሶስት ወር የሚስተናገዱበት አሰራር ተግባራዊ መደረጉን አስረድተዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት