ቀደም ሲል የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት ከሎጀስቲክስ አንጻር አምራች ኢንዱስትሪዎችን ታሳቢ ያደረገ ደንበኛ ተኮር አገልግሎት እየሰጠን ነው ፡፡
ሚያዝያ 28/2017(ኢሚ) በሶስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አራተኛ ቀን ውሎ "በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊና ቅንጅታዊ አሰራር የአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ በሪሶ አመሎ(ዶ/ር)፤ ወደብ የደረሰ ገቢና ወጪ ምርት ከስምንት ቀን ባጠረ ጊዜ የማጓጓዝ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ በተደረገው ጥረትም የሎጂስቲክስ አገልግሎቱን ለማሳለጥ ከተለዩ 790 ድርጅቶች ውስጥ ለ509 አምራች ኢንዱስትሪዎች ልዩ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት