ከኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ቅሬታ በአፋጣኝ ለመፍታት ሙሉ በሙሉ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን ለመተግበር እየሰራን ነው፡፡
ሚያዝያ 28/2017(ኢሚ) በሶስተኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አራተኛ ቀን ውሎ "በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተቋማዊና ቅንጅታዊ አሰራር የአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነትና ተወዳዳሪነትን ማሳደግ" በሚል መሪ ሀሳብ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ከኃይል መቆራረጥ ጋር ተያይዞ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ቅሬታ በአፋጣኝ ለመፍታት ሙሉ በሙሉ የዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥን ለመተግበር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በተለይም ለአምራች ኢንዱስትሪው በተመጣጣኝ ዋጋ የኃይል አቅርቦት በመስጠት ለሀገር ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዲወጡ እየተደረገ ነው ብለዋል።
የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ማዕከላትንና ማስተላለፊያ መስመሮችን በማዘመን የኃይል አቅርቦት መቆራረጥ ችግሮችን መቀነስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውቀዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት