የኢትዮጵያ ታምርት ማህበረሰቡ በሀገሩ ምርት እንዲኮራ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው ፡፡ (ወ/ሮ አበባ ታመነ)
ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ለሶስተኛ ጊዜ በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 በመጨረሻ ቀን የውይይት መርሃ ግብር ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚዋ ወ/ሮ አበባ ታመነ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ማህበረሰቡ በሀገሩ ምርት እንዲኮራ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው።
ስራ አስፈፃሚዋ አክለውም በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 5ኛና የመጨረሻ ቀን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ውጤታማና ዘመኑ የሚጠይቀውን ጥራት ያሟላ ምርት ባለቤት በመሆን ዓለማቀፍ ተወዳዳሪነቱን እና ተፈላጊነቱን ያረጋገጠ እንዲሆን ለማስቻል የሚታዩ ክፍተቶችን በማሳየት ከአምራቾች ጋር የቅርብ ውይይት በማድረግ ጉድለቶቹ የሚሞሉበትን መፍትሄ በመጠቆምና በሀገራችን ምርት የመጠቀም ባህላችንን በማሳደግ ዘርፉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ጊዜውን የዋጀ የአሰራር ስርዓት መጠቀም እንዲችል መስራት የሁላችንም ሀገራዊ ኃላፊነት መሆን አለበት ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት