ሀገራዊ ብልጽግናን ዕውን ለማድረግ ቀድመን ባልሰራናቸው ስራዎች ከመቆጨት ባሻገር ባሉን የወደፊት መልካም ዕድሎች ተስፋ በመጣል ተግተን መስራት አለብን (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በ3ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የመጨረሻ ቀን የፓናል ውይይት መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ያደጉ ሀገሮች የደረሱበትን የብልጽግና ደረጃ ለመድረስ ቀድመው ባልተሰሩ ስራዎች ከመቆጨት ባሻገር ያሉንን የወደፊት መልካም ዕድሎች ለመጠቀም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ቴክኖሎጅን ማህከል ያደረገ አሰራርን በመዘርጋት በትጋት መስራት ይገባል ብለዋል።

ሀገራዊ ክብራችንን ለማስጠበቅ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ውጤታማ ስራ መስራት ብቸኛ አማራጭ ነው ያሉት አቶ ታረቀኝ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ቅልጥፍናንና ምርታማነትን ለመጨመር በየደረጃው ለአምራች ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post