አምራች ኢንዱስትሪዎች ለባለሙያዎቻቸው የክህሎት ስልጠና የሚያባክኑትን ጊዜ ለማስቀረት እየተሰራ ነው ፡፡ (ዶ/ር ኮራ ጦሽኔ)
ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ትምህርት ሚንስትር ደኤታ ዶ/ር ኮራ ጦሽኔ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ በቂ ክህሎት ያለውን ተግባራዊ ባለሙያ መፍጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሚንስትር ደኤታው የዩንቨርስቲ ተመራቂዎች ተግባራቸውን በብቃት ማከናወን እንዲችሉና አምራች ኢንዱስትሪዎችም ለክህሎት ስልጠና የሚያባክኑትን ጊዜ ለማስቀረት ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲና ኢንዱስትሪ ትስስር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
አሁን ላይ ያሉት አምራች ኢንዱስትሪዎች በተለመደው አሰራራቸው ቢቀጥሉ ተወዳዳሪ መሆን አይችሉም ያሉት ዶ/ር ኮራ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅመው ከወቅቱ ጋር የሚራመዱ ብቁ ባለሙያዎች ሊኖሯቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በመጨረሻም አሁን ላይ እንደ ድሮው ጽንሰ ሀሳብ ብቻ የሚያውቅ ሳይሆን በተግባራዊ ልምምድ ክህሎቱን ያዳበረ መምህርና ተማሪ ለመፍጠር ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው እየተጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት