እያንዳንዱ አምራች ኢንዱስትሪ የራሱን ችግር በራሱ ለመፍታት በቋሚነት የጥናንትና ምርምር ስራዎችን መስራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡ (ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ)

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪና ምርታማ ስለሚሆኑበት ሁኔታ ማብራሪያ የሰጡት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ አምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪ ሆነው ለመቀጠል በአሰራር ሂደት የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶችን በራሳቸው አቅም ለመፍታት መጣር አለባቸው፡፡

እያንዳንዱ አምራች ኢንዱስትሪ ችግሮችን ለመፍታት በቋሚነት የጥናትና ምርምር ስራዎችን መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታማና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ተቋማቸው ለሰው ኃይል ልማት ትኩረት መስጠቱን በመጥቀስ የተመራማሪዎችን አቅም ለመገንባት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡

ከትምህርት ስርዓቱ ጋርም ተያይዞ ቀደም ሲል የነበሩ ክፍተቶችን ለመሙላት ከዘመናዊ ዕሳቤ ጋር የተቆራኘ ባለሙያ ለመፍጠር ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post