ቴክኖሎጅን መጠቀም የህልውና ጉዳይ ነው (ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ)
ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በ3ኛው ዙር ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምስተኛ ቀን የፓናል ውሎ ቴክኖሎጅን ከምርት ጋር በማዋሀድ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማዘመን በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡
በውይይት መርሀ ግብሩ በፓናሊስትነት የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስትር ዶ/ር የሽሩን አለማየሁ በዚህ ዘመን ቴክኖሎጂን መጠቀም ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የህልውና ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ዶ/ር ይሹሩን ቴክኖሎጂን በአግባቡ መጠቀም ያልቻሉ ሀገሮችም ሆነ አምራች ኩባንያዎች ከውድድር ውጭ መሆናቸውን በመጥቀስ የአምራች ኢንዱስትሪውን አሰራር ዲጂታል ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎችን አሰራር ለማዘመን ከቴክኖሎጅ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ጀምሮ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎች የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት