ተመራቂ ተማሪዎች አዲስ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ እንጂ ነባር ዕውቀቶችን ብቻ ተሸካሚ እንዳይሆኑ እንሰራለን ፡፡ (ዶ/ር ደረጀ እንግዳ)

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በ3ኛው ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ አምስተኛ ቀን የፓናል ውይይት የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች አዲስ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ ስለሚሆኑበት ሁኔታ ማብራሪያ ተሰጠ፡፡

በፓናሊስትነት ተሳትፈው ማብራሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ ተመራቂዎች አዲስ ቴክኖሎጂ ፈጣሪ እንጅ ፅንሰ ሀሳብ ብቻ ተሸካሚ እንዳይሆኑ ዩኒቨርስቲያቸው ተግቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍና ለማዘመን ታስቦ እንደተቋቋመ ያብራሩት ፕሬዜዳንቱ ቀደም ሲል የነበሩ ሀገር በቀል ክህሎቶችን በቴክኖሎጂ በማገዝ ዘርፉን ለማዘመን በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ደረጀ ዩኒቨርስቲው ከካሪኩለም ቀረጻ አኳያም የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንዲሆን አምራች ኢንዱስትሪዎችን ያሳተፈ ቀጣይነት ያለው ውይይት እያካሄደ ነው ብለዋል፡፡

በየጊዜው የሚከሰቱ ኢንዱስትሪ ነክ ተግዳሮቶችንም ለመፍታት ዘላቂነት ያላቸው ጥናትና ምርምሮች እየተካሄዱ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post