የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት "መሀሉ ዘመን" በሚል በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ተወያዩ ።
ሚያዚያ ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራር እና ሰራተኞች "የመሀሉ ዘመን" " በሚል በተዘጋጀው ሀገራዊ ሰነድ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በውይይት መድረኩን ላይ ባደረጉት መክፈቻ ንግግር ዜጎች ሃገራቸው ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ የሀገሪቱን ፓሊሲዎች ፣ስትራጂዎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ማወቅ እና መገንዘብ አለባቸው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም የመንግስት ሰራተኛው የኢትዮጵያ ብልፅግናና ሁለንተናዊ እድገትን ተገንዝቦ የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ማበርከት እና የተሰጠውን ሃገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል ፡፡
የውይይት ሰነዱን ያቀረቡት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አክሊሉ ታደሰ በበኩላቸው ሀገሪቱ ላይ በፊትና ከለውጡ በኋላ የነበሩ ፈተናዎች የታለፈበት ሂደት፣ በሰባት አመታት ውስጥ የታዩ ኢኮኖሚያዊ ስኬቶች እና ውድቀቶች የሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ፣በአለም አቀፉ ደረጃ የመጡ ለውጦች፣ አስመልክተው ማብራሪያ ተሰጥተዋል ፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሀገሪቱ ባለፋት አመታት ያጋጠማትን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን በመቋቋም አስገራሚ የእድገት ደረጃ ላይ መደረሷ የሚበረታታ መሆኑን በማንሳት በቀጣይም ከመንግስት ጎን በመቆም የሀገርን ሰላም እና ኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል ፡፡