የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን እንዲቀንሱ አድርጓል፡፡ (አቶ ጥላሁን ዓባይ)

ግንቦት1/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ዓባይ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተሰራ ቅንጅታዊ ስራ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መቀነስ እንደ ተቻለ ገልፀዋል ፡፡

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልልና ከተማ አስተዳደርና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ጥላሁን መንግስት አምራች ኢንዱስትሪው ለሌሎች ዘርፎች የጀርባ አጥንት እንዲሆን በትኩረት እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ስራ አስፈጻሚው ለውጭ ምርቶች የገበያ መዳረሻን ከማስፋት አንጻር ባለፉት የበጀት ዓመቱ 9 ወራት ብቻ ለስድስት ተጨማሪ ሀገራት ምርት መላክ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚፈልጉትን ማነኛውንም አይነት አገልግሎት በዲጅታል አሰራር ባሉበት ሁነው የሚስተናገዱበት ሁኔታ መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post