የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ ነው :: (አቶ ሀሰን መሐመድ )
ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የግብዓትና መሠረተ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሀሰን መሐመድ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የተሰጠው ትኩረት ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ ስለመሆኑ በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የታዩ ተግባራት ምስክር ናቸው ብለዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በልዩ ሁኔታ የተቋቋመው የብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል የዘርፉን ችግሮች በደረጃ በጥናት በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ እየሰጠ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀሰን የኢትዮጵያ ታምርት ክላስተር በክቡር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና በክልል ምክትል ፕሬዘዳንቶችና ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባዎች እየተመሩ የዘርፉን ማነቆዎች በመፍታት ዘርፉ እድገት የህልውናችን ጉዳይ መሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ስለመሆኑ ዋና ዋና ማሳያዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል ።
ዘርፉን ወደ ፊት በስኬት በማስፈንጠር የተያዘለትን ሀገራዊ የእድገት አበርክቶ እንዲያሳካ ሁላችንም በየተሰማራንበት ዛሬ መስራት የምትችለውን ነገር ለነገ አትተው የሚለውን መርህ በተግባር ማሳየት ሀገራዊ ሃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት