ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ማስፋፋት ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠል የሞት ሽረት ጉዳይ መሆን አለበት ፡፡ (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)
ግንቦት 01/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ማስፋፋት ሀገርን እንደ ሀገር ለማስቀጠል የሞት ሽረት ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብና ለሌሎች በማስገንዘብ የተጀመረውን ንቅናቄ ባለበት ግለት ለማስቀጠል ሁሉም ባለድርሻ አካል ቁርጠኛ መሆን አለበት ያሉት የዕድገትና ተወዳዳሪነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ የዘርፉን እቅዶች ከግብ ለማድረስ ሌት ከቀን እንቅልፍ አጥተን መስራት ትውልድ የሰጠን አደራ መሆኑን አውቀን ልንተጋ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
አቶ ታረቀኝ አክለውም አንዳችን ከአንዳችን ያለንን መልካም አፈፃፀም እንደ ተሞክሮ ወስደን ወደ ተግባር በመቀየርና ክፍተቶችን ለይተን የጋራ የመፍትሄ አቅጣጫ እያስቀመጥን ለመስራት ከተጋን የማናሳካው እቅድ የለም ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት