በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን ክፍተት በመለየት በድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ እንሰራለን፡፡ (አቶ መላኩ አለበል)

ግንቦት 02/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከተጠሪ ተቋማት ጋር የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪዎች የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም በገመገሙበት ወቀት እንደገለፁት ለዘርፉ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ የዘርፉን አስፈፃሚ ባለድርሻ አካላት አቅም በመገንባት፣ መሰረተ ልማቶችን በማሟላት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር በመስራት የሀገራችንን አምራች ኢንዱስትሪ በአፍሪካ ተወዳዳሪና ተምሳሌት እንዲሆን መስራት አለብን ብለዋል ።

በሁሉም አካባቢዎች ያሉ ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን ክፍተት በመለየት በድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን ያላቸውን ፀጋ ሐይቶ በመጠቀም ውጤታማ ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም ሁሉም የ2017 ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም የ2018 ዕቅድ ከፌደራል ተቋም ጋር ተናበው እንዲሰሩ ፣ የኢትዮጵያ ታምርት አደረጃጀት ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲሰራ አና የተቀላጠፈ አገልግሎት እንዲሰጡ እና ውሳኔ ለሚሰፈልጋቸው ጉዳች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት የዘርፉን እቅድ ለማሳካት በትጋት መስራት እንደሚጠበቅ በማሳሰብ የስራ አቅጣጫ ተሰጥተዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post