መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የውጭ ሀገር ባለሃብቶችን ለማበረታታት ምቹ ፖሊሲና ስትራቴጅ ቀርጿል:: (አቶ ሀሰን መሀመድ)

ግንቦት 8/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብአት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ አድቫንስድ ከትሬንድ ኤንድ ማይኒንግ (ADVANCED TRADE AND MINING) ድርጅት ተወክለው የመጡ የኳታር ባለ ሀብቶችን ተቀብለው አወያዩ፡፡

አቶ ሀሰን በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሚሰማሩ የውጭ ባለሀብቶች መንግስት ምቹ ፖሊሲና ስትራቴጅ መቅረጹን ለባለ ሀብቶቹ ገልጸዋል፡፡ ባለሀብቶቹ በግብርናና በማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ሲሆን የግብርናና ማዕድን ውጤቶች ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ በዋናነት ለግብዓትነት የሚያገለግሉ መሆናቸውን ጠቅሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሚመለከታቸው ሌሎች ባለድርሻ መስሪያ ቤቶች ጋር በመቀናጀት የሚጠበቅበትን ድጋፍ እንደሚያደርግ ሚኒስትር ደኤታው አብራርተዋል፡፡

የትሬንድ ኤንድ ማይኒንግ ድርጅት ተወካዮችም በበኩላቸው የሚጠበቅባቸውን መስፈርት አሟልተው በቶሎ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post