የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን በዓለም አቀፍ ገበያ በጥራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው፡፡ (አቶ ፀሐዬ ይነሱ)

ግንቦት 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሀገሪቱ እድገትና ልማት የሚያበረክተውን ወሳኝ አስተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው ምርቶች መካከል አንዱ የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርት መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ሥራ አስፈፃሚ የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ዴስክ ኃላፊ አቶ ፀሐዬ ይነሱ ገልፀዋል ፡፡

በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በመለየት ምርትና ምርታማነታቸውን እንዲያያሻሽሉ ‘’በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ’’ በተለያየ ደረጃ ካሉ ባለድርሻ አካላት በፈጠረው መነቃቃትመሰረት በዘርፉ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ በቅንጅት በመስራት በጋራ ችግሮችን የመፍታት፣ ስራዎችን በተናበበ ሁኔታ ተፈጻሚ የማድረግ እና የመፍትሄ አካል ሆኖ በመረባረብ ረገድ በዘርፉ ውጤት መታየቱን አስረድተዋል፡፡

በአገራች ያሉት ኢንዱስትሪዎች መረጃ በተጠናከረ መልኩ በመሰብስ እና በክልሎችና በከተማ መስተዳድር ለሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ክትትልና ድጋፍ በማድረግና ለሚያጋጥመሟቸዉ ማነቆዎች በጋራ የመፍታት ስራዎች መሰራተቻውን ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ሀገር ውስጥ ያልተተኩ የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶችን ለመተካትና አምራች ኢንዱስትሪዎቹ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚሰጡ የጥራት ደረጃዎችን እንዲያሟሉ የግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ምርቶቻቸውን በጥራትና አቅርቦት በማሳደግ ከኢትዮጵያ ገበያ አልፎ ኤክስፖርት እንዲያደርጉ ድጋፍ እየተደረገ ነው ያሉት አቶ ፀሐዬ በምርቶች ግብዓትና ባለቀለት ምርት ላይ ያሉ የታክስ አሰራር ስርዓቶችን ለማስተካከል ሚኒስቴር መስራያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለስልኮች ፣ለሞባይል ቻርጀር፣ ለዋይፋይ ራዉተር እና ለሲምካርድ አምራች ኢንዱስትሪዎች የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉንም ተናግረዋል፡፡

ለትራንስፎርምር፣ ለኤሌትሪክ ፖል፣ ለኤሌክትሪክ ሜትር፣ ለኬብልና ዋየር አምራቾች በተፈጠረላቸው የገበያ ትስስር ምርቶቻቸውን ለተለያዩ ቦርድ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ መቻሉን ያነሱት የዴስክ ኃላፊው በኬብልና ዋየር አምራች ኢንዱስትሪውች እና በኮበር ሮድ አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከልም የግብዓትና የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post