መንግስት ቆዳ የኤክስፖርት አማራጭና የኢንዱስትሪያላይዜሽን ዋና ዘርፍ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው(አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)

ግንቦት15/2017 ዓ.ም(ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ 14ኛውን የመላ አፍሪካ የቆዳ ንግድ ትርኢትን ከፈቱ፡፡

አዲስ አበባ በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄደውን የቆዳ ምርቶች ዐውደ ርዕይ የከፈቱት አቶ ታረቀኝ መንግስት ቆዳን የኤክስፖርት አማራጭና የኢንዱስትሪያላይዜሽን ዋና ዘርፍ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

ሚንስትር ዴኤታው አፍሪካ በእንስሳት ሀብት ፀጋ የታደለች መሆኑን ጠቅሰው የአፍሪካ ሀገራት ከቆዳ ማግኘት ያለባቸውን ተገቢ ጥቅም እንዲያገኙ ወደ ውጭ ከሚላኩ ምርቶች ዕሴት የመጨመር ስራ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ለቆዳው ኢንዱስትሪ በቂ መሰረተ ልማት፣ገብዓት አቅርቦትና በቂ የሰለጠነ የሰው ሀይል አለመኖር ማነቆ ሁኖ መቆየቱን አውስተው አሁን ላይ መንግስት የዘርፉን ችግር ለመፍታት የቆዳ ኢንዱስትሪ ስትራቴጅ ቀርጾ እየሰራ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በቆዳው ኢንዱስትሪ ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ለዘርፉ መሪ ሆነው በህብረት እንዲያድጉ በአህጉር ደረጃ ተናበውና ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

ዐውደ ርዕዩ ቀደም ሲል የነበሩ የቆዳ ምርት ጥራትና የማምረት አቅም ችግሮች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት ምን ያህል እየተቀረፉ እንደ መጡ የሚያሳይ መሆኑን በተጎበኙ ምርቶች ማወቅ ተችሏል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post