የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በኢትዮጵያ የቤልጀየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲቼልን በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ::

ግንቦት 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢንዱስትሪ መሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በኢትዮጵያ የቤልጀየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲቼል በቢሯቸው ተቀብለው አነጋገሩ::

ቤልጂየም እና በኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው ያሉት አቶ ሀሰን መሀመድ ሁለቱ ሀገራት የዘላቂ ልማት እና የኢኮኖሚ ለውጥ የጋራ ራዕይ እንዳላቸው ተናግረዋል ፡፡

የቤልጂየም ኩባንያዎች በእውቀታቸው፣ በፈጠራቸው እና በአለምአቀፍ በየነ መረብ ግንኘኙነቶች(networks) የኢንዱስትሪ ምርቶቻችንን በማሳደግ ረገድ የለውጥ ሚና ስለሚጫወቱ በጋራ መስራቱ አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

መንግስት በተለይም እንደ አግሮ ፕሮሰሲንግ እና ቴክኖሎጂ ባሉ ዘርፎች የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ ምቹ የንግድ ሁኔታን ለመፍጠር ቁርጠኛ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

እሴት መጨመርን፣ ጥራትን ማሻሻል እና የገበያ መስፋፋትን የኢትየጵያ መንግስት ያበረታታል ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው የቤልጂየም ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ስነ-ምህዳር ውስጥ ፈጠራን እና ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በመሳተፍ ኢንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡

በኢትዮጵያ የቤልጀየም አምባሳደር ዶ/ር አኔሊስ ቨርስቲቼል በበኩላቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እየተደረገ ያለው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተግባር ለሀገር ዕደገት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ዘርፉን ለማሳደግ በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post