ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍን በመደገፍ እና ችግሮችን በመፍታት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቋቋመ ነው ( አምባሳደር ግርማ ብሩ)

በአምባሳደር ግርማ ብሩ የሚመራው ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሚስተዋሉ ችግሮች ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

በውይይቱ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ተጠቅመው እንዳያመርቱ የሚያደርጉ እና ለውጤታማነታቸው እንቅፋት ናቸው በተባሉ ምክንያች ዙሪያ የተዘጋጀ ሰነድ የቀረበ ሲሆን የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶችም ተገኝተው ያጋጠሟቸውን ችግሮች ለካውንስሉ አቅርበዋል፡፡

በማክሮ ኢኮኖሚው ማሻሻያ የመጡ እድሎችን በመጠቀም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባም የብሔራዊ አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ሰብሳቢ አምባሳደር ግርማ ብሩ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ አያይዘውም ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስሉ ዘርፉን በመደገፍ እና ችግሮችን በመፍታት ተወዳዳሪ ለማድረግ የተቋቋመ ኮሚቴ መሆኑን አክለው ከፋይናንስ ተቋማት፣ከሎጀስቲክ ፣ከገበያና ግብዓት ትስስር እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር በተያየዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post