የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ድርሻ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ ነው (አቶ ሀሰን መሐመድ)

አዲስ አበባ ግንቦት 25/2017 (ኢ•ሚ) የኢትዮ ቤልጄም ቢዝነስ ፎረም ተካሄደ፡፡

የኢትዮ ቤልጄም ቢዝነስ ፎረም ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማትና ግብዓት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሃመድ ኢትዮጵያ ለኢንዱስትሪያላይዜሽን ያላትን የማያወላውል ቁርጠኝነት እና በለውጥ ሂደቷ፣ በቅንጅት እና በጠንካራ መሰረት የተገነባ ትብብር ስርዓትን እውን ማድረግ የለውጥ ተስፋችን ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።

የኢትዮ ቤልጄም ቢዝነስ ፎረም መካሄድ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ እና ዘላቂ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመከባበር ፣ በጋራ ምኞቶች እና ገንቢ ትብብር ላይ የተመሰረተ አጋርነት መሆኑን ያረጋግጣል ።

ሁለቱን ሀገራት ለዘላቂ ልማትና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የጋራ ራዕይ ያላቸው መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀሰን በፈጠራ፣ በዘላቂነት እና በንግድ ስራ ውጤታማነት የቤልጂየምን ዓለም አቀፍ አመራር እናደንቃለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ የ10 ዓመት ሀገራዊ የልማት እቅድና የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ወደ ኢንዱስትሪያላይዜሽን እና ዘላቂ እድገት እያደረገች ላለው ለውጥ መሰረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የቢዝነስ ፎረሙ በተለያዩ ስትራቴጂካዊ ዘርፎች ያለንን የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወቅታዊ እድልን ይሰጣል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በተለይ ማኑፋክቸሪንግ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለመቀየር ቅድሚያ የተሰጠው ዘርፍ መሆኑን ገልፀዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ ድርሻ ከፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ማሻሻያዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ፈንታ ከማኑፋክቸሪንግ ጋር የተያያዘ በመሆኑ በዘርፉ መሰማራት ከሚፈልግ ማነኛውም ሀገር ጋር በቁርጠኝነት እንደምትሰራ በመግለፅ ቤልጅየማዊያን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እንዲሰማሩ ኢትዮጵያ ጥሪዋን ታቀርባለች ብለዋል፡፡

Share this Post