አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ምርትና ምርታማነቱን ለመጨመር የአመራር አቅም ግንባታ ወሳኝ ነው(አቶ ሃሰን መሃመድ)

ግንቦት 26/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መረሃ ግብር የበቃ ኢንዱስትሪ አመራር ለላቀ ተወዳሪነት በሚል መሪ ቃል አምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል ለተመረጡ 50 ተፅዕኖ ፈጣሪ ኢንዱስትሪዎች ተለይተው የአመራር አቅም ግንባታ የትግበራ ማስጀመሪያ መድረክ ተካሄደ ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ እንደገለፁት አምራች ኢንዱስትሪ የዘርፉን ተወዳዳሪነትን ለማሳደግና ምርትና ምርታማነቱን ለመጨመር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

አዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እንዲቀረጽና ለፖሊሲው ተግባራዊነት የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና መርሃ-ግብሮችን በመቅረጽ ወደ ሥራ እንዲገባ በመደረጉ ዘርፉን ወደፊት የሚያራምዱ በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

በተለይም መንግስት የዘርፉን ችግር በቅርብ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ “ብሔራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ካውንስል” በማቋቋም ቁልፍ የሆኑ ባለድርሻ አካላት እየተገናኙ በሚያደርጉት ክትትልና ግምገማ የዘርፉን ችግሮች በመቅረፍ ምርትና ምርታማነት እንዲሁም የመምራት አቅም አጠቃቀም እየጨመረ መጥቷል ብለዋል፡፡

“የበቃ ኢንዱስትሪ ለላቀ ተወዳዳሪነት” በሚል መሪ ሃሳብ የተጀመረው የኢንዱስትሪዎቻችን የአመራር ጉዳይ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን አውቀንና ተረድተን ለመርሃ-ግብሩ ተፈፃሚነት ሁላችንም የድርሻችንን በቁርጠኝነት ልንወጣ ይገባል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ አመራር ሥርዓት ፍተሻ ከተለዩት 252 ለውጥ አምጭ (Game Changers) ኢንዱስትሪዎች በፓይለት ደረጃ በ50 ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚጀመር መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሀሰን ከእያንዳንዱ ንዑስ ዘርፍ አሥር አሥር ኢንዱስትሪዎችን በመለየት የሚጀመር ሲሆን የኢንዱስትሪ አመራር ሁለንተናዊ ማሻሻያ ፕሮጀክት አድርገን የምናየው ይሆናልም ብለዋል፡፡

የኢንዱስትሪ አመራር ማሻሻያ ድጋፍን እንዲያስተባብሩ ሚኒስቴር መ/ቤታችን አመራሮችን በመመደብ፣ ከሚመለከታቸው የምርምር ማዕከላት መሪ ቡድንና የትግበራ ቡድኖችን በማደራጀት 36 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ተደራጅቶ ሥልጠና ወስደው ለሥራው ዝግጁ ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ባለሙያዎች ወደ ኢንዱስትሪዎች ሲመጡ የኢንዱስትሪ ባለቤትና አመራሮች ለዚህ ጥናት ተገቢውን መረጃ በመስጠት ለተግባሩ ስኬታማነት በባለቤትነት ስሜት ሥራውን እንዲቀበሉ አሳስበዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post