ኢንዱስትሪ ለአንድ ሃገር ቁልፍ ጉዳይ ነው(ኢንጅነር ምንዳዬ ይርጋ)

ግንቦት 26/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ የአመራር አቅም ግንባታ መርሃ ግብር የጥናት ሰነድ ያቀረቡት የካይዘን ኢንስቲትዩት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ምንዳዬ ይርጋ እንደገለፁት የአንድ ሃገር ኢንዱስትሪ ውጤታማና ተወዳዳሪ የሚሆነው በፈጠራና በቴክኖሎጂ እድገት ፤ የሰለጠነ የሰው ሃይል አጠቃቀም፤ የተግባር ልህቀት እና ቅልጥፍና ፤ የተደራጀ የአቅርቦት ሰነሰለት፣ ደንበኛ ተኮር ስራና ተደራሽ ገበያ ሲኖረውእንዲሁም አለማቀፋዊ ደረጃዎች አሟልቶ ሲገኝ ነው ብለዋል ፡፡

ማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪው ለአንድ አገር ወሳኝ ነው በዚህም የኢንዱስትሪውን ሥነ ምህዳር ለማሻሻል መንግስት አዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ እንዲቀረጽና ለፖሊሲው ተግባራዊነት የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና መርሃ-ግብሮችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ እንዲገባ በመደረጉ ዘርፉን ወደፊት የሚያራምዱ በርካታ ውጤቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ በዋነናት ዓላማው የግል ሴክተሩን ወደ ተሻለ ምርታማነት ማሳደግ እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርት እንዲመርት የተሻሻሉ የኢንዱስትሪ አመራር ልምዶች እንዲያዳብር በቢዝነስ አስተሳሰብ እና ባህል በሰለጠነ እውቀት የሚመራ እንዲሆን ለማስቻል ነው ብለዋል ፡፡

የኢንዱስትሪዎችን አጠቃላይ ግምገማ በማካሄድ ለኢዱስትሪዎች ተግባራዊ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ደረጃ በደረጃ በመለየት እንደሚሰጥ ዋና ስራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡

የኢንዱስትሪ የአመራር አቅም ግንባታ መርሃ ከ(50) ሃምሳ ኢንዱስትሪዎች 100 የኢዱስትሪ ባለቤቶች እና ስራ አስኪያጆች እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ከ150 በላይ የኢንዱስትሪ ዘርፉ መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ባለሃብቶቹ በቀረበው ሰነድ ላይ እና በስራቸው እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮችን ያነሱ ሲሆን በዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽ ተሰጥቷቸዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post