የክልል አመራሮች በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አቅም ያላቸውን የውጭ ኢንቨስተሮች ለመሳብ አበክረው መስራት አለባቸው(አቶ መላኩ አለበል)

ግንቦት 28/2017 ዓ.ም(ኢሚ) የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለሚገኙባቸው አራት የክልል መስተዳደሮች የመኪና ርክክብ ስነስርዓት አካሄደ፡፡

በርክክብ ስነስርዓቱ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የክልል አመራሮች በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ አቅም ያላቸውን የውጭ ኢንቨስተሮች ለመሳብ አበክረው መስራት እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመኪና ድጋፉን ያደረገው ከጣልያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ(Italian Agency For Developmente Cooperation)ጋር በመተባበር ሲሆን ለኦሮሚያ፣ አማራ፣ ሲዳማና ትግራይ ክልሎች አንዳንድ አበርክቷል፡፡

የመኪና ስጦታው ዋና ዓላማ አራቱም ክልሎች በስራቸው የሚገኙት የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚያከናውኑትን የምግብ ላብራቶሪ ፍተሻ፣ የልህቀት ማዕከል ግንባታና ስልጠናዎችን ተዘዋውረው የድጋፍና ክትትል ሰራዎችን መስራት እንዲችሉ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post