የመንግስት ማንኛውም ኢኮኖሚዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ አካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረገ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)
ግንቦት 28/9/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ ፅዱ ኢትዮጵያን ባህል ማድረግ በሚል መሪ ቃል የተካሄደውን ሁለተኛውን የአካባቢ ብክለት መከላከል አገራዊ ንቅናቄ የመስጀመሪያ መርሐ ግብር ፓናል ውይይት ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለፁት ማንኛውም ኢኮኖሚዊ ማህበራዊ እንቅስቃሴ አካባቢ ጥበቃን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን በመጥቀስ የአረንጋዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የኮሪደር ልማት፣ የወንዞች ዳርቻ ልማትና የፓርኮች ልማት በሃገራችን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች የሚጠቀሱ ናቸው ብለዋል ፡፡
በሃገራች የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ዘላቂ ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም ገልፀዋል ።
በሌላ በኩል የአካባቢ ጥበቃ ምክትል ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ፍሬነሽ መኩሪያ እንደገለፁት ሁነቱ በአለም ለ52ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ32 ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካባቢ ብክለት መከላከል ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን ፖሊሲ ቀርፃና በአዋጅ ደንግጋ እየሰራች ከህዝብ ቁጥር መጨመርና ከከተሞች መስፋፋት ጋር በተያያዘ የአካባቢ ብክለት፣ የደኖች መመናመን፣ የወንዞች መበከል በአጠቃላይ በተፈጥሮ ሃብታችንና በሃገራችን ላይ ስጋት እየፈጠሩ መሆናቸውን በመጥቀስ ሁሉም ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት