አምራች ኢንዱስትሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በዘርፉ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች ወሳኝ መሆናቸው ተገለጸ

ግንቦት 28/2017 ዓ.ም(ኢሚ) በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የምርምርና ቴክኖሎጅ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍቃዱ አሸኔ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የግድ በጥናትና ምርምር መደገፍ እንዳለባቸው ገልፀዋል ፡፡

ዶ/ር ፍቃዱ አምራች ኢንዱስትሪዎች በየወቅቱ የሚገጥሟቸውን ተግዳሮቶች በዘላቂነት ለመፍታት ኢንስቲትዩቱ በአራት መስኮች ትኩረት ሰጥቶ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ በአረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ምርትና የአመራረት ስርዓትን በማሻሻል ዙሪያ፣የግብይት አቅምን ከማሳደግ አኳያና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የአዋጭነት ጥናትና ምርምሮችን እንደሚያካሂድ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አማካኝነት እየተሰሩ ያሉ ጥናትና ምርምሮች የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀምንና ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ በተጨማሪ ምቹ የገበያ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ ከፍተኛ ውጤት ማምጣታቸውንና ገቢ ምርቶችንም በሀገር በቀል ምርቶች በስፋት የሚተኩበትን ዐውድ መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post