የጉሎ ዘይት በአለም አቀፍ ደረጃ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው እፅዋት ነው(አቶ ሃሰን መሃመድ )
ግንቦት 28/9/2017ዓ.ም (ኢሚ) ጆርጅ ሹ ኀ.የተ የግ.ማ ከዚህ ቀደም የራሱን ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገንባት በኢትዮጵያ በቆዳ፣ ጫማና በኮንስትራክሽን ስራ ተሰማርቶ የሚገኝው ካፓኒ ነው ፡፡
አሁን ላይ በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን የጉሉ ዘይት ፋብሪካ በመገንባት ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ከግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጣይ ሊሰራ በሚችልበት ሁኔታ ዙራያ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ እንደገለፁት የጉሎ ዘይት ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው በማንኛውም አይነት የአየር ፀባይ የሚበቅል በሃገራችን በሁሉም ክልሎች በስፋት ያለ ድርቅን የሚቋቋም መደበኛ ባልሆነ ዝናብ ወቅት ሊበቅል የሚችል የአፈርን ለምነት እና እና የውሃ የመያዝ አቅመ የሚጨምር እና ተለዋዋጭ የአየር ንብርት ለወጥ እንዳኖር የራሱን አስተዋፆኦ የሚያደርግ እፅዋት ነው ብለዋል ፡፡
በቀጣይ ይህ የጉሎ ዘይት በሃገራችን በስፋት እንዲመረት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን የተመለከተ ግንዛቤ የመፍጠር እና ስራውን የማስፋት ስራ ይሰራል ብለዋል ፡፡
በሌላ በኩል የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) የግብርና ሚኒስቴር ዘርፉን የሚደግፉ እቅዶች እና ስትራቴጂዎች በማዘጋጀት አሁን ላይ ፖሊሲዎችን እየከለስን ኢንዱስትሪያል አላማ ላላቸው ስራዎች ኮንትራት ፋርሚንግ በማዘጋጀት በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሀብቶች በቀላሉ ወደ ስራ ገብተው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል ፡፡
በመጨረሻም ጆርጅ ሹ ኀ.የተ የግ.ማ ምክትል ፕሬዝደንት ቺው ጃን ቹን እንደገለፁት ስራ በጀመሩ በአጭር ጊዜ 20 ኮንቶነር የጉሎ ዘይት ወደ ቻይና በመላክ 1ሚሊየን ዶላር እንዳገኙ ገልፀው ወደፊት በስፋት ለመስራት እና ውጤታማ ለመሆን እንደሚሰሩ ገልፀው የመንግስት ድጋፍ እንዳይለያቸው አሳስበዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት