የአምራች አዱስትሪው አቅም አጠቃቀም መለካት ለሃገራዊ ኢኮኖሚዊ ዕድገት እና ልማት ወሳኝ ነው (አቶ ዮናታን ተስፋዬ)
ሰኔ 3/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለክልል እና ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ፣ ለአምራቾች ፣ ለተጠሪ ተቋማት እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ላይ የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ።
ስልጠናውን የሰጡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ማዕከል ተመራማሪ አቶ ዮናታን ተሰፋዬ እንደገለፁት የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ስርዓት እንደ ሃገር ከሌለ የምናስበውን ዘላቂና ውጤታማ የአመራረት ሰርዓት በማምጣት ተወዳዳሪና ደረጃውን የጠበቀ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ምርት ለማምረት እንቅፋት ይሆንብናል ሲሉ ገልፀዋለ ።
በሃገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ፓሊሲ እና መመሪያ ተቀርፆ ወጥቷል ያሉት ተመራማሪው የአሰራር ሰርዓቱን በሚገባ አውቀንና ተረድተን መስራት አለብን ብለዋል ።
የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ሰንል ልኬት፣ ስራው የሚሰራበት መንገድ፣ የሚወጣበት አቅም ፣ እና በመጨመር እና በመቀነስ የሚነሱ ጉዳዮች ሲሆኑ ሌሎችም ለሰራው አሰፈላጊ የሆኑ ጉዳዮች የሚገቡ ይሆናሉ ብለዋል ።
አቶ ዮናታን ተሰፋዬ የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ ጠቀሜታ አዋጭ የአሰራር ሰርዓት ፣ ኢኮኖሚያዊ ጤናማነት ፣ የዋጋ ግሽበትን መቆጣጠር እና በተጨማሪ የድርጅቱን አጠቃላይ ውጤት በሃገር ኢኮኖሚ ላይ ለመለየት እና ለመወሰን አቅም ይሆናል ብለዋል ።
የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ የአንድን ችግር ስረመሰረት በመረዳት መፍትሔ ለመስጠት ወሳኝ በመሆኑ የትኛውም ዘርፍ ለተግባራዊነቱ ትኩረት ሊሰጥ ይገባልም ብለዋል።
የማምረት አቅም አጠቃቀም አለካክ የአንድን ሃገር ኢኮኖሚ ውጤታማነት ለመገምገም እና በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት አስፈላጊ እና ችግርና መፍትሔ አመልካች ተግባር ነው ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት