ምርታማነት ውጤታማ የሚሆነው ጊዜን፣ ጉልበትንና ካፒታልን አጣጥሞ መስራት ሲቻል ነው ( አቶ ዮናስ መኩሪያ )

ሰኔ 3/2017ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ምርታማነት ምንድን ነው በሚል ፀንሰ ሃሳብ ከክልል እና ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ፣ ለአምራቾች ፣ ለተጠሪ ተቋማት እና የኢዱስትሪ ሚኒስቴር ሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።

ስልጠናውን የሰጡት የኢትዮጵያ ታምርት የአቅም ግንባታ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ዮናስ መኩሪያ እንደገለፁት ምርታማነት ደበኞችን ታሳቢ ያደረገ ጥራት እና ጊዜን መሰረት አድርጎ አለም አቀፍ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ተመራጭ እና ተወዳዳሪ የምርት ስርዓትንመከተል መከተል ነው ብለዋል ።

የምርታማነት ዋና ጉዳይ ግብዓት እና ውጤት ሲሆን ይህን በሚፈለገው ልክ ለማሰኬድ የጊዜ አጠቃቀም ፣ ቴክኖሎጂ ፣ የሰራተኞች ክህሎት ፣ጤናማ የስራ አካባቢ እና የስራ ደህንነት ወሳኝ ናቸው ብለዋል ።

ምርታማነት በግል፣ በቢዝነስ ወይም በሀገር ደረጃ ለእድገት ቁልፍ ነገር ነው ያሉት አቶ ዮናስ መኩሪያ መንግስት በዘርፋ ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ ለዘርፉ እድገት የሚጨነቁ የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ የሚተጉ ብቁ ተመራማሪዎችን መርጦ ተልዕኮ በመስጠት ወደ ተግባር የሚቀየር ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ።

ምርታማነትን በማሳደግ የሀገራችንን ኢንዱስትሪ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ ስራዎችን በፖሊሲዎችንና ስትራቴጅዎች አፈፃፀም በየጊዜው ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን መገምገምና እያሻሻሉ በመስራት ወቅቱ የሚጠይቀውን ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post