የተኪ እና የውጪ ምርቶችን ውጤማነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው (አቶ መሳይነህ ውብሸት)

ሰኔ 4/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ የተኪ ምርት ስትራቴጂ ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያላቸው ኢንዱስትሪዎች፣ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው ።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት እንደገለፁት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ ስትራቴጂ በማዘጋጀት በዋናነት የተኪ እና የውጪ ምርቶችን ውጤማነት ለማሳደግ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው።

በመሆኑም የሀገር በቀል ኢኮኖሚውን ለማሻሻል የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ትልቁን ድርሻ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመረዳት በዘርፉ የሚስተዋለውን ችግሮች መፍታት የሚችል ባለሙያዎችን ለመፍጠር አቅም የማሳደጉ ተግባር በተጠናከረ መልኩ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎችን በእውቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በተኪ ምርት ስትራቴጂ ዙሪያ ሥልጠና ተዘጋጅቶ እየተሰጠ መሆኑን እንደማሳያነት ገልፀዋል፡፡

አቶ መሳይነህ አክለውም በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የምርት ጥራትን በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ገበያ ጥራትና ተወዳዳሪነት ለማሳደግ ስትራቴጂዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግባቸው አስረድተዋል::

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post