የተኪ ምርት ስትራቴጂ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት እና ለማጠናከር ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና አለው።
ሰኔ 4/2017 ዓ.ም (ኢሚ) በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም በተገቢው መንገድ በመረዳትና በመጠቀም ረገድ የተኪ ምርት ስትራቴጂው ውጤት ማሳየቱን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ዴስክ ኃላፊ ወ/ሮ መሰሉ አበበ ገልፀዋል ።
ስትራቴጅው የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት እና ለማጠናከር ለሚደረገው ጥረት ጉልህ ሚና አለው ያሉት ኃላፊዋ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ተወዳዳሪነት በማበረታታት የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ፣ ፈጠራን እና ለአምራች ኢንዱስትሪው እሴት መጨመርን የሚያበረታታ ሥነ-ምህዳር መፈጠሩ ለውጤታማነቱ ምክንያት መሆኑ አስረድተዋል ።
በስትራቴጂው መነሻ የሀገር ውስጥ የአምራች ኢንዱስትሪ ምርቶችን በኢንጂነሪንግ እና በቴክኖሎጂ ዘርፎች በመለየት ድጋፍ በማድረግ ውጤታማነቱን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል የአካባቢና ደህንነት( Environmental and safety) ዴስክ ኃላፊ አቶ ይደርሳል ደሳለኝ በበኩላቸው የሀገር ውስጥ አቅምን ከማሳደግ በዘለለ ኢኮኖሚው ከዓለም አቀፍ ገበያ መለዋወጥ ለመጠበቅ እና ከውጭ የኢኮኖሚ እና የገበያ ቀውስ ተጋላጭነትን ለመቀነስ ስትራቴጂው እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን ዕድገት በማጎልበትና ተወዳዳሪነትን በማሳደግ የሀገር ውስጥ ፍላጎት በማሟላት የወጪ ንግድ በማሳደግ ዘርፋ የሃገራችን ኢኮኖሚ ወደ ብዝሃ የኢኮኖሚ ስብጥር የሚውስድ መሆኑን ገልፀዋል ።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት