አምራች ኢንዱስትሪዎች ቀጣይነት ያለው ዕድገት ኖሯቸው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የደንበኞቻቸውን ፍላጎት የሚያሟላ ምርት ማምረት አለባቸው ።
ሰኔ 5/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት፣ ከጂ አይ ዜድና ሶሊዳሪዳድ ጋር በመቀናጀት ለሀያ ጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካ ተወካዮች በብሔራዊ የተቀናጀ የምርት ጥራት መቆጠጠሪያ ስርዓት(National Integrated Production Quality Management System) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፡፡
በስልጠና መርሀ ግብሩ የጨርቃጨርቅና አልባሳት አምራች ኢንዱስትሪዎች ቀጣይነት ያለው ዕድገት ኑሯቸው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የገዥዎቻቸውን ፍላጎት ሊያሟላ የሚችል ጥራት ያለው ምርት ማምረት እንዳለባቸው ተጠቅሷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሁሉንም ዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛዎች የሚያሟላ የጥራት ደረጃ የቁጥጥር ስርዓት መከተል እንዲችሉ ማድረግ ስለመሆኑ ተገልጿል፡፡
ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በይዘቱም የተቋም ነባራዊ ሁኔታን መለየት፣ የምርት ጥራት ደረጃን የሚያስጠብቅ የአመራር ዘዴ፣ የምርት ጥራት ደረጃ ለመቆጣጠር ማቀድ፣ ድጋፍ አሰጣጥ፣ የደምበኞችን ቅሬታ ማስተናገድ፣ በጥራት መመዘኛ መስፈርቶችን ተከትሎ መስራት፣ አፈፃፀምን መገምገምና የጥራት ማሻሻያ ዘዴዎችን የሚመለከቱ ጉዳዮች ይዳሰሱበታል ፡፡
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ብሔራዊ አካታች የምርት ጥራት ደረጃ የቁጥጥር ስርዓት መመሪያ ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት