የቀርቀሃና የእንጨት ውጤቶች ሀገራዊ ፋይዳቸው ዘርፈ ብዙ ነው ( አቶ መሳይነህ ውብሸት)

ሰኔ 6/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ክራኬቲቭ ካታሊስት ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ በእንጨት፣ በቀርቀሃ እና በጥሬ ዕቃ ማምረቻ እሴት ሰንሰለቶች ላይ በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ሚነስቴር የተኪ ምርቶች ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት እና ክራኬቲቭ ካታሊስት ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ት ናዝራዊ እንዳለ ናቸው ፡፡

በፊርማው ስምምነቱ ወቅት አቶ መሳይነህ ውብሸት እንደገለፁት የቀርቀሃና የእንጨት ውጤቶች ለሀገር ኢኮኖሚዊ ልማት እና በስራ ዕድል ፈጠራ እና በውጭ ምንዛሪ ግኝት ከፍተኛ አስተዋፆኦ ያላቸው በመሆኑ ስምምነቱ እንደ ሀገር ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የዘርፉን ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት የሚያስችል የተግባር አፈፃፀም በማዘጋጀት በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የውጭ ምንዛሪ በማዳን፣ ከአካባቢ ልማት ጋር የተጣጣመ ኢንቨስትመንት በማስፋት፣ በሀገር ውስጥ ያለው ስትራቴጂያዊ አቅም በመጠቀም እየሰራን ያለነው ስራ አካል ነው ጠቀሜታው የላቀ ነው ብለዋል ፡፡

ወ/ት ናዝራዊ እንዳለ በበኩላቸው ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽኦ ማበርከት በሚያስችል ሁኔታ አምራች ኢንዱስትሪዎቻችን ጋር አብሮ ለመስራት እድሉን በማግኘታቸው ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን በመጥቀስ የእንጨት ውጤቶች እና የቀርቀሃ ውጤቶች አምራቾች፣ ከፈርኒቸር ግብዓት አምራቾች፣ ከንዑስ ዘርፉ የግብዓት አስመጪዎች እና የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ጋር በቅርበት በመነጋገርና አብሮ ለመስራት የሚያስችል ዕቅድ በመንደፍ ወደ ስራ እገባለን ሲሉ ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post