ሙስናን ለመግታት ከታችኛው መዋቅር እስከ ፌዴራል ድረስ ተቋማት በቅንጅት መስራት አለባቸው(ወ/ት ኤልሳቤጥ በየነ)
ሰኔ 7/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማትና ከክልል የኢንዱስትሪ ቢሮዎች ጋር የስነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ፎረም ምስረታ አካሄደ፡፡
የፎረሙን ምስረታ አስመልክቶ ገለፃ ያቀረቡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ኤልሳቤጥ በየነ ሙስናን ለመግታት ከታችኛው መዋቅር እስከ ፌዴራል ድረስ ተቋማት በቅንጅት መስራት አለባቸው ብለዋል።
የፎረም ምስረታው ዋና ዓላማ በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያሉ የክልልና የፌደራል ተቋማት የስራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን የሞራል ዕሴት መገንባት መሆኑን ስራ አስፈፃሚዋ ገልፀዋል ፡፡
በመርሀ ግብሩ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በስሩ ካሉ ተጠሪ ተቋማትና ከክልል የኢንዱስትሪ ቢሮዎች ጋር ተቀናጅቶና ተናቦ በመስራት በዘርፉ ላይ ብልሹ አሰራሮች እንዳይኖሩና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የተለያዩ ስልቶችን እየቀየሰ የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን እንደሚሰራ ተብራርቷል፡፡
በመጨረሻም ተአማኒነት፣የሙያ ብቃት፣የአሰራር ጥንቃቄ፣የጋራ ስራዎች ከተቋሙ ዓላማ ጋር የሚሄዱ መሆኑን ማረጋገጥ፣የተጠናከረ አደረጃጀት፣በቂ በጀት መመደብና ውጤታማ የተግባቦት ክህሎትን መተግበር የዘርፉ ተቋማት በጋራ ሲሰሩ ሊተሏቸው የሚገቡ መርሆዎች መሆናቸውን መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ወ/ት ኤልሳቤጥ ገልጸዋል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት