የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፉን መልካም ስነ ምግባርን በተላበሱ አመራሮች መመራት ለምርታማነትን ቁልፍ ድርሻ አለው (አቶ ሀዱሽ ሀለፎም)
ሰኔ 7/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ጥሩ ስነ ምባር መላበስ ምርታማነትንና የማምረት አቅምን እንደሚያሳድግ ገለጹ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባካሄደው የስነ ምባርና ፀረ-ሙስና ፎረም ምስረታ መርሀ ግብር ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ሀዱሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች በስራቸው ያሉ ባለሙየዎችን የስራ ተነሳሽነት ለማሳደግ ፣የምርት ብክነትን ለማስቀረትና ያላቸውን ሀብት በተቢው ቦታ አውለው የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር ጥሩ ስነ ምባር በተላበሰ አመራር መመራት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡
የሚንስትር ጽ/ቤት ሀላፊው ሙስና በዓለም ከሚታዩ ጦርነቶችና የተፈጥሮ አደጋዎች ተለይቶ እንደማይታይ በመጥቀስ ችግሩ በአመራር ሰጭ አካላት ብቻ የተወሰነ ሳይሆን በሁሉም ባለሙያ ሊከሰት የሚችል ነገር ስለሆነ ለግል ጥቅም ብሎ ከመስራት በመቆጠብ ሀገራዊ ፍቅር የሰፈነበት አሰራር መከተል እንደሚገባ ገልፀው የፎረሙ ዓላማ ግቡን እንዲመታ ያላሳለሰ ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ቀደም ሲል ከሁሉም የክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስተትሪ ቢሮዎች ጋር በፀረ-ሙስና ዙሪያ በቅንጅት ለመስራት የስምምነት ሰነድ የተፈራረመ ስለመሆኑ ተገልጿል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት