ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎቹን አስገመገመ፡፡

ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢፌዲሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የሥነ ምግባር ግንባታ እና የሙስና መከላከል ስራዎቹ በፌደራል የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን የድጋፍና ክትትል ቡድን ግምገማ አካሄደ ፡፡

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም የ2017 በጀት ዓመት የ4ኛውን ሩብ ዓመት የድጋፍና ክትትሉ ዓላማ በስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስራዎች ላይ የሚታዩ የአተገባበር ክፍተቶችን እንዲስተካከሉ ለማድረግና የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን ደግሞ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለማስቻል የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በክትትልና ድጋፉ በዘርፉ የተሻለ አፈፃፀም የተገኘ ቢሆንም ለቀጣይ እንዲስተካከሉ የተሰጡ አስተያየቶችን ትኩርት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

በተለይም ዘርፉን ለማሳደግ ከክልልና ከተማ አስተዳደር ጋር የተጀመሩት የስነ-ምግባር ግንባታ እና ሙስና መከላከል ስራዎች እና ቅንጅታዊ አሰራር ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post