የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ በዘርፉ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ዙሪያ ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል። (ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ)

ሰኔ11/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ፡፡

የስልጠና መርሀ ግብሩን በንግግር የከፈቱት የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አመራሮች ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ በዘርፉ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ዙሪያ ጥልቅ የሆነ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ስልጠናውን የሰጠው ለሰባት ዩኒቨርስቲዎች፣ ለክልልና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም በአዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና ስትራቴጅዎች ዙሪያ የዘርፉ አመራሮች ግልጽና የጠራ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል መሆኑን ተጠቅሰዋል፡፡

በስልጠናው መርሀ ግብር ለአዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ መቀረጽ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተና ስለ ፖሊሲው አስፈላጊነት በስፋት ተብራርቷል፡፡

ቀደም ሲል የነበረው ፖሊሲ በዘርፉ የሀገር ውስጥ የባለሀብቶችን ድርሻ ከማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች ከመተካት፣ ከምርት ተወዳዳሪነትና ዝርዝር የማስፈጸሚያ ፕሮግራሞችን ከማካተት አንፃር ውስንነት እንደ ነበረው ተገልጿል፡፡

በአንፃሩ አዲሱ ፖሊሲ በግብርና ምርቶች ዕሴት መጨመር ላይ ትኩረት አድርጎ መቀረጹ ኤክስፖርትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተብራርቷል፡፡

በአዲሱ የአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና የማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎች ዙሪያ የተጀመረው ስልጠና ለሁለት ቀናት ይቀጥላል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post