የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለማሳደግ ለማሽነሪ ኢንዱስትሪ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።
ሰኔ11/2017 ዓ.ም (አ/ሚ) የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በሚሰጠው የፖሊሲና ስትራቴጅ ስልጠና መርሀ ግብር ተገኝተው የማሽነሪ ስትራቴጅን በተመለከተ ገለፃ ያቀረቡት የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ መሳይነህ ውብሸት ዘርፉን ለማሳደግ ለማሽነሪ ኢንዱስትሪ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በዓለም በማሽነሪ ኢንዱስትሪ ውጤታማ የሆኑ ሀገራት ከፍተኛ የምርት ግብዓት አስገቢና ኤክስፖርተር መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ መሳይ ኢትዮጵያም ከውጭ ከምታስገባቸው ማሽነሪዎች የተለያዩ ዕሴቶችን በመጨመር ከራሷ ፍጆታ አልፋ ኤክስፖርት የምታደርግበት ምቹ ሁኔታ እንዳለ አብራርተዋል፡፡
ስራ አስፈፃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ ለማሽነሪ ኢንዱስትሪ ባለቤት የሆኑ መንግስታዊ ተቋማት፣ ጠንካራ የዘርፍ ማህበራትና ሰፊ የውስጥ ገበያ መኖሩ ምቹ ሁኔታ ስለሆነ ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት አጠቃላይ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገትና በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው አስረድተዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት