የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለአምራች ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪነት የሚጨምሩት ፋይዳ ሊኖር ይገባል

ሰኔ12/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ)የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲና ማስፈጸሚያ ስትራቴጅዎች ዙሪያ ለሁለት ቀናት የሰጠው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በስልጠናው መጨረሻ የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃጋማ በዘርፉ ተመራማሪዎች የሚሰሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት አንዳች ፋዳ ሊያመጡ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር ሚልኬሳ የጥናትና ምርምር ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ኢንስቲትዩቱ ራሱን የቻለ የአሰራር ስርዓትና መመሪያ እንዳዘጋጀ አብራርተዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ በኢንስቲትዩቱ ስር ያሉ የጥናትና ምርምር ማዕከላት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ጥሩ ሰርቶ ማሳያዎች ይሆኑ ዘንድ ተቋማቸው ብቃት ያላቸውን በርካታ ተመራማሪዎች ለማፍራት የሰው ሀይል ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የክልልና ከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች ከጥናትና ምርምር ማስኬጃ ጋር ተያይዞ የሚገጥማቸውን የበጀት ችግር ለመቅረፍ ከዩኒቨርስቲዎች ጋር ከመቀናጀት ባሻገር ጥራትና ብቃት ያለው ፕሮፖዛል ቀርጸው ከዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች ሀብት የማፈላለግ ስራ መስራት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post