ፋብሪካው በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ስኩዌር በላይ ፎርም ወርክ ማምረት ይችላል፡፡

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ)የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ስኩዌር በላይ ፎርም ወርክ የማምረት አቅምም ያለው በመሆኑም የኮንስትራክሽን ዘርፉን የፎርም ወርክ ፍላጎት በአስተማማኝ ደረጃ ማሟላት እንደሚችል የኤች ኬ ቢዝነስ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካሳነሽ አያሌው ገልፀዋል።

ፋብሪካው የዘመኑን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም እና ምንም አይነት ወደ ከባቢ የሚለቀው ፈሳሽ ወይም ጠጣር በካይ ነገር የለውም ያሉት ስራ አስፈፃሚዋ ለዚህ ዘላቂ ችግር መፍትሄ ፍለጋ በሚል ያደጉ ሀገራትን ተሞክሮዎች በመውሰድ ይህ ዘመናዊ ፋብሪካ ተገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቀዋል፡፡

ምርቱ ከፍተኛ ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም ለሥራ ቅልጥፍና ምቹ መሆኑና ከአካባቢ ጋር ምንም አይነት ተቃርኖ የሌለው መሆኑ ከሌሎች ፎርም ወርክ ይለያል ብለዋል።

የፎርም ወርክ ምርቶች የማይከብዱ እና ጥንካሬያቸው አስተማማኝ በመሆኑ ለኮንክሪት ሥራዎች ተመራጭ እንደሚያደርጋቸውም ጠቁመዋል፡፡

ፎርም ወርኩ የአገልግሎት ጊዜውን ሲጨርስ ፋብሪካው ያንን አገልግሎቱን የጨረሰ ምርት ተቀብሎ ለዳግም አገልግሎት እንደሚያውለውም ገልጸዋል፡፡

በተለይ ለሕንፃና ለድልድይ ግንባታዎች ሊያገለግል እንደሚችል ያስረዱት ወ/ሮ ካሳነሽ ይሄውም በአካባቢ ላይ ሊከሰት የሚችለውን ብክለት ከማስቀረት በተጨማሪ ለገንቢዎች የሚኖረው ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ የላቀ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post