ሃገራዊ ዕድገትን የምናረጋግጠው አምራች ኢዱስትሪውን በመደገፍ ነው (አቶ መላኩ አለበል)
ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ፈቃዱ ፀጋዬ ቢዝነስ ግሩፕ የቤት እቃዎች እና የመኪና ሞተር መገጣጠሚያ፤ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል መርቀው ከፈቱ፡፡
ሚኒስትሩ በምረቃው መርሃ-ግብሩ ላይ እንደገለፁት መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ሃገራዊ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ከፍ እንዲል ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል ፡፡
ኤክስፖርትን ማበረታታት፤ ገቢ ምርት መተካት፤ ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ፤ የማምረት አጠቃቀምን ማሳደግ እና አዳዲስ ኢንቨስትመንት መሳብ መንግስት አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚዊ አበርክቶ ከፍ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራባቸው ካሉ ስራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል ፡፡
የሃገርን ዕድገት የምናረጋግጠው በእውቀት ላይ ተመስርተን ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ የምንሰራቸው ስራዎች አለም አቀፍ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ እና ተወዳዳሪ መሆን ሲችሉ ነው ያሉት አቶ መላኩ የምርታማነት ዋና ጉዳይ ግብዓት እና ውጤት ሲሆን ይህን በሚፈለገው ልክ ለማስኬድ የጊዜ አጠቃቀም፣ ቴክኖሎጂ ፣ የሰራተኞች ክህሎት፣ ጤናማ የስራ አካባቢ እና የስራ ደህንነት ወሳኝ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ኢንዱስትሪ ያለ መንግስት በየትኛውም አለም ዕውን ሆኖ አያቅም በዚህም መንግስት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ለመወጣት እና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገራችንን ኢንዱስትሪ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ለማድረግ ስራዎችን በፖሊሲዎችንና ስትራቴጅዎች አፈፃፀም በየጊዜው ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን መገምገምና እያሻሻሉ በመስራት ወቅቱ የሚጠይቀውን ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በመጨረሻም የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ዕድገታችን የኢትዮጵያን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ እንደ ተግዳሮት የሚታዩትን የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ክፍተቶች በመለየት ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
በምረቃ ስነ-ስረዓቱ ላይ የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊዎች እና የከተማዋ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት