ቢሾፍቱ ከተማን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ እና የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራን ነው ( አቶ አለማየሁ አሰፋ )

ሰኔ13/10/2017 ዓ.ም (ኢሚ) ቢሸፍቱ ከተማ በባህልና በቱሪዝም መስህብ የበለፀገች ከመሆኗ ባለፈ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት እያስመዘገበች መሆኑን የቢሸፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ ገለፁ ፡፡

ቢሾፍቱ ከተማ በፍጥነት እያደጉ ካሉ የኢትዮጵያ ከተሞች አንዷ ስትሆን በውስጧ ከ1,900 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋሞች ያሏት መሆኑን ከቲባው አቶ አለማየሁ አሰፋ ገልፀዋል ፡፡

አነስተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎችን ከኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የቅርብ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ምርትና ምርታማነቱን ለመጨመር የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረግን ነው ብለዋል ፡፡

በዚህም በከተማችን የነበረው የኢንዱስትሪ የአፈፃፀም አቅም ከ40 በመቶ ወደ 68 በመቶ አድጓል ያሉት ከንቲባው በ2017 ዓ.ም ከ60 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች አዲስ የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉንና የከተማዋ ገቢ ከ1ቢሊየን ብር ወደ 10 ቢሊየን ብር ከፍ ማለቱን ገልፀዋል ፡፡

ወደፊት ከዚህ በላይ በመስራት ቢሾፍቱ ከተማን የኢንዱስትሪ የቱሪዝም ማዳረሻ በማድረግ ለኗሪዎቿ ምቹ ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post