የአምራች ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የሚያደርጉላቸው ድጋፍና ክትትል እንደ ሚያበረታቸው ገለጹ

ሰኔ 17/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ፋብሪካዎችን ጎበኙ፡፡

በጉብኝታቸው አግኝተው ያነጋገሯቸው የኢንዱስትሪ ባለሀብቶች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያደረገላቸው ያለውን ድጋፍ በማመስገን የዘርፉ ከፍተኛ አመራሮች የሚያደርጉላቸው ክትትል እንደሚያበረታቸው ተናግረዋል፡፡

ሚንስትሩ ጉብኝቱን ያካሄዱት ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዜዳንት ዶ/ር እመቤት መለሰና ከአዳማ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ጋር ሲሆን የጉብኝቱ ዋና ዓላማም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከገንዘብ ብድር አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ግብአት ለማሰባሰብ ስለመሆኑ ተገልጿል ።

አቶ መላኩ ባለ ሀብቶችን በተናጠል እያገኙ ያለባቸውን ተግዳሮት በተመለከተ ካወያዩ በኋላ ሁሉም አምራች ኢንዱስትሪዎች ከዋናው የምርት ተግባራቸው ጎን ለጎን ኢንዱስትሪያቸውን የሚጎበኙ ጎብኝዎች እየተዝናኑ ስለ ዘርፉ ዕውቀት የሚገበዩበት ሁኔታ እንዲፈጠር በግቢያቸው ምቹ የማረፊያና የመዝናኛ ቦታ ማዘጋጀት እንዳለባቸው ጠቁመዋል፡፡

ጉብኝት የተካሄደባቸው ፋብሪካዎች ኬ አይ ቲ፣ ሌግዠሪ፣ ካም ሴራሚክስ፣ አፍሪ ስካይ፣ ዲና፣ አዳማ ቆርቆሮ ፋብሪካና ገብሬ ጉርሙ የእንጨት ስራዎች ናቸው።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post