ለአለም አቀፍ ሁነቶቹ መሳካት ሚስጥር በመናበብና ጠንክሮ በመስራት ነው (የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል )
ሰኔ 18/2017 ዓ.ም (ኢሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በበላይነት ሲመራቸው ለነበሩ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት አስተዋፅኦ ላደረጉ የሚዲያ ተቋማት እና ባለድርሻ አካላት የእውቅና እና ምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል።
በ2017 በጀት አመት እንደ ሀገር ከተካሄዱ አለም አቅፍ ሁነቶች መካከል አንዱ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አቅጣጫ ሰጪነት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አስተባባበሪነት ከረሃብ ነፃ አለም በሚል በጥቅምት ወር የተካሄደው አለም አቀፍ ኮንፈረንስ መሆኑን የገለፁት የኢንዱስትሪ ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ይህም ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም፣ የግብር፣ ማኑፋክቸሪግ እና የቴክኖሎጂ ማስፋፋትና የሽግግር አቅማችንን ማሳየት የቻልንበት ኮንፈረንስ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።
116 ሀገራት ተሳታፊ የሆኑበት ይህ ኮንፈረንስ ኢትዮጵያ የኮንፈረንስ ቱሪዝምን ለማከናወን በቂ አቅም እንዳላት ያሳየም ጭምር ነው ያሉት አቶ መላኩ አጀንዳው ለመሪዎችና ለልማት አጋር አካላት ለውሳኔ ሰጪነት የሚያግዛቸውና ለቀጣይ እቅድ የሚሆኑ መነሻ ሃሳቦች የተገኘበት ነው ሲሉ አክለዋል።
ሌላኛው ትልቁ ሁነት ለ3ኛ ጊዜ የተካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2017 ሲሆን በዚህም የእምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን የማምረት አቅም በማሳደግና አቅሙን በማሳየት ፣ የተኪ ምርት በማሳደግ ፣ ከፍተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠር ፣ የአምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት እንዲያደርግ እና በትልቁ ገጽታችንን የገነባንበት ነው ያሉት አቶ መላኩ ለዚህም የሚመለከታቸው ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች እንዲሁም ባላድርሻ አካላት ርብርብ የጎላ እንደነበር ገልፀዋል።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የመጀመሪያ ሶስት አመታት ጉዞ ስለ ንቅናቄው ምንነት አጠቃላይ መረጃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ ሚና የጎላ ነው ሲሉ የገለፁት ሚኒስትሩ ግንዛቤ የመፍጠር ስራው ከእቅዱ አንፃር የተሳካ እንደሆነ አክለዋል።
በአጠቃላይ ለሁለቱ አለም አቀፍ ሁነቶች መሳካት የድሻቸውን ለተወጡ የተቋማት አመራርና ሰራተኞች፣ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ዘርፍ አመራርና ባለሞያዎች እንዲሁም ባላድርሻ አካላት ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት