ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ' የተባለውን መጤ አረም ለሲሚንቶ ማምረቻ በኃይል አማራጭነት መጠቀም የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገባ

ሰኔ 21/2017(ኢሚ) በሳይንሳዊ ስሙ 'ፕሮሶፒስ ጁሊ ፍሎራ' የተባለውን መጤ አረም ለሲሚንቶ ማምረቻ በኃይል አማራጭነት ለመጠቀም ሲደረግ የነበረው ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር ገብቷል።

መጤ አረሙን ወደ ኃይል በመለወጥ ለሲሚንቶ ማምረቻነት ለማዋል እንዲቻል በተደረገ ጥናት ላይ ውይይትና የልምድ ልውውጥ ዛሬ በድሬዳዋ ተካሂዷል።

'ፕሮሶፒስ' በመባል በአጭሩ የሚጠቀሰው መጤ አረም በኢትዮጵያ በአብዛኛው ተደጋጋሚ ድርቅ በሚከሰትባቸው አካባቢዎች በስፋት ተንሰራፍቶ ይገኛል።

አረሙ በአፋርና ሶማሌ ክልሎች በብዛት ተንሰራፍቶ ሲገኝ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎችም በተወሰኑ አካባቢዎች ይገኛል።

በኢትዮጵያ በጠቅላላው በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ ተንሰራፍቶ የሚገኘው አረሙ በተለይ በሶማሌና በአፋር ክልሎች የግጦሽና የእርሻ መሬትን በመውረር ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post