ከፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም የፀዱ መሬቶች ዓመቱን በሙሉ በሰብል መሸፈን አለባቸው(አቶ ዳዊት አለሙ)
ሰኔ22/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) ፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም ከፀዳ በኋላ እንደ ገና ስለሚበቅል የፀዱ መሬቶችን ዓመት እስከ ዓመት በሰብል መሸፈን እንዳለባቸው በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፐርፎርማንስ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አለሙ ገለጹ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የልምድ ልውውጥ ሰሚናር ላይ አጠቃላይ ፕሮጀክቱ ያለበትን ሁኔታ አስመልክቶ ገለፃ ያቀረቡት አቶ ዳዊት አረሙን እንደ ሀይል አማራጭነት ለመጠቀም እየተሰራ ባለው ስራ በሄክታር ከ13 እስከ 20 ቶን ባዮ ማስ ማምረት እንደ ተቻለ ተናግረዋል፡፡
በጠቅላላ በሙከራ ፕሮጀክቱ ሀያ ዘጠኝ ሽ ሁለት መቶ ሀያ ስድስት ቶን ባዮ ማስ የተመረተ ሲሆን አረሙ በነበረባቸው ቦታዎችም የአካባቢው ገበሬዎች የተለያዩ ምርቶችን እያመረቱባቸው መሆኑን አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም በፕሮጀክቱ ዙሪያ የግሉ ዘርፍ ተጨማሪ ማሽኖችን በማስገባት ከፍ ያለ አቅም ፈጥሮ በቅንጅት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት