የስሚንቶ ፋብሪካዎች አማራጭ ሀይልን ለመጠቀም ዝግጁ መሆን አለባቸው(ኢ/ር አክሱማዊ ዕቡይ)

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም(ኢ/ሚ) የፓን አፍሪክ ግሪን ኢነርጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አክሱማዊ ዕቡይ ሀገሪቱ የጀመረችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕውን ለማድረግ ሁሉም አምራች ኢንዱስትሪ አማራጭ ሀይልን ለመጠቀም ዝግጁ መሆን እንደሚገባው ገልፀዋል ፡፡

ከአየር ንብረት ብክለት የጸዳ የአመራረት ስልትን መጠቀም ከማህበረሰብ ጤና ባሻገር የኢኮኖሚ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ያስረዱት ኢንጅነር አክሱማዊ ስሚንቶ ፋብሪካዎች ባዮ ማስን መጠቀም እስካሁን ለነበረባቸው ችግር ዋና መፍትሄ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢንጅነሩ በፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ አረም ሊደርስ የሚችለውን ሀገራዊ ጉዳት ለማስቀረትና የውጭ ምንዛሬ እጥረትን ለመቅረፍ ብሎም ተስማሚ የአየር ንብረት እንዲኖር ለማድረግ አምራች ኢንዱስትሪዎች በባለቤትነት ስሜት ተቀናጅተው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post