የኢትዮጵያ እና የኳታር ግንኙነት ለሰላም፣ ለብልፅግና እና ዘላቂ ልማት በጋራ ራዕይ ላይ የተመሰረተ ነው ( አቶ ሃሰን መሃመድ)
ሰኔ 23/2017ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን መሃመድ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት የኳታር መንግስት ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሳድ ቢን ሙባረክ አል ናይሚ በፅፈት ቤታችው ተቀብለው አነጋገሩ ፡፡
አቶ ሃሰን መሃመድ እንደገለፁት ኢትዮጵያ እና ኳታር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሃገሮች እንደ መሆናቸው ባላቸው የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በባህል፣ በትምህርት፣ በህዝቦቻችን መካከል ያለው ትስስር እየዳበረ መጥቷል ሲሉ ገልፀዋል ።
በተለያዩ የጋራ ጥቅሞቻችን ትብብራችንን ለማጠናከር እና ለማስፋፋት አዳዲስ መንገዶችን ለመፈተሽ እና ለጋራ ጥቅም እና ዘላቂ እድገት በጋራ እሰራለን ብለዋል ፡፡
አቶ ሃሰን መሃመድ ኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ፤ ግብርና፤ ቱሪዝም ኢንቨስትመንት ትልቅ አቅም ያላት ሃገር እንደመሆኗ ለስራው ምቹ ፖሊሲ እና ስትራቴጂ በመቅርፅ እየሰራን እንገኛለን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡
በተጨማሪም መንግስት ከፋይናንስ ተቋማት፣ ከሎጀስቲክ፣ከገበያና ግብዓት ትስስር እንዲሁም ከመሰረተ ልማት ጋር በተያየዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየሰራበት ይገኛል ብለዋል ፡፡
በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር እና በአፍሪካ ህብረት የኳታር መንግስት ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ሳድ ቢን ሙባረክ አል ናይሚ በበኩላቸው ስለተደረገላቸው ገለፃ አመስግነው በኢትዮጵያ ያሉትን የኢንቨስትመንት ዕድሎች ምቹ እና ሳቢ በመሆናቸው ያሉትን እድሎች ለመጠቀም እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል ፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት